አስኳላ: 11 በ 1

ትምህርታዊ ጨዋታዎች

የመጪው ጊዜ ትምህርትቤትዎ

ይጫወቱ . ይሳተፉ . ይማሩበጥራት የተሰሩ ቀላል እና ተወዳጅ ኢትዮጵያዊ ጨዋታዎች

እጅ ጽሁፍ

የአማርኛ ፊደላትን በቀላሉ መጻፍ ለመለማመድ ያስችላል። የፊደሎች ድምጽ እና ቅርጽን ለመለየት እና ልምምድ ለማድረግ ያግዛል። ጨዋታው በቀላሉ ፊደላትን መጻፍ እንዲችሉ ሆኖ የተዘጋጀ ነው

የፊደል ገበታ

የአማርኛ የፊደል ገበታ ዋና ፊደላት የተካተቱ ሲሆን፤ እያንዳንዳቸውን ፊደሎች ቅርጽ ፣ ቅደም ተከተል እና ድምጽ መለየት እንዲያስችል ሆኖ የተዘጋጀ ነው

አዛምድ

በጨዋታው በግራ በኩል ያሉ ፊደላት በቀኝ በኩል የተመለከቱ ቃላት (እቃዎች፣ እንሰሳት ፣ ስም ፣ .ወዘተ) የመጀመሪያ ፊደል ሲሆኑ ትክክል የሆኑትን በመለየት በመስመር ያገናኙ

ባቡሬ

ባቡሩ ላይ በቅደም ተከተል መሠረት የጎደለውን ፊደል ይሙሉ። ቅደም ተከተሉ በአማርኛ የፊደል ገበታ ዋና ቤቶች ወይም ሰባቱ የአግድም ቤቶች ቅደም ተከተል ሊሆን ይችላል

የት አለሁ

በጨዋታው የሚሰማውን የፊደል ድምጽ ካሉ አማራጮች መካከል ይለዩ። ጨዋታው የፊደላትን ድምጽ የመለየት አቅምን በእጅጉ ያሻሽላል

ዳሽ ሙላ

በጥያቄነት የቀረበን ቃል የሚያሟላ ፊደል ከቀረቡት ምርጫዎች ውስጥ ይምረጡ። ይህንን በማድረግም የቃላት እውቀቶን ያሳድጉ ፣ ፊደላት በቃላት ውስጥ ያላቸውን የድምጽ ሚና ይለዩ ፣ ፊደላትን በአግባቡ ይለዩ

እንቆቅልሽ

በአጫዋች ተርታ ያሉ ፊደሎችን ከመጫወቻ ሜዳው ካሉት ጋር ያጣምሩ

የቁጥር ሰሌዳ

የግዕዝ ቁጥሮችን ቅርጽ እና ድምጽ ለመየት የሚያችል ሰሌዳ

ቁጥር አዛምድ

ልማዳዊ ቁጥሮችን ከግዕዝ ቁጥሮች ጋር ያዛምዱ

ቁጥሩን ያያችሁ

የአጫዋቹን ድምጽ ሰምተው ከአማርጮች ውስጥ ቁጥሩን ይምረጡ

ፉርጎ፡ የቁጥር ባቡር

በባቡሩ ላይ ካሉ ተርታ ቁጥሮች የጎደለውን አንድ ቁጥር ወደ ባቡሩ ይጫኑ


ከሞባይል ስልኮች እና ታብሌቶች የሚጣጣምሳቢ ዲዛይን. ቀላል. አሳታፊ ጨዋታዎች.

አስኳላ በተለያዩ ጥራት እና መጠን በሚገኙ የአንድሮይድ እና የአይፎን ስልኮች እና ታብሌቶች ላይ የፒክሰል-ፍጹም እይታ እና የተጠቃሚ ተሞክሮ እንዲኖረው በጥሩ ሁኔታ ተገንብቷል

ለአስኳላ ደረጃ ይስጡ

ለራስ ልጆች ማስተማሪያነት የተሰራህጻናት የተሳተፉበት የማበልጸግ ሂደት

ከ 3 እስከ 9 ዓመት ያሉ ህጻናት ልጆች የልማት ቡድኑ አለቆች ናቸው። ልምዶቻቸው እና አስተያየቶቻቸው በደንብ ተሰብስበው ማሻሻያዎች ተደርገዋል። ለተከበሩ ልጆቻችን እርካታ እና የመማር ምቾት የማሻሻል ስራችንን እንቀጥላለን

ከአፕ ስቶርያውርዱከፕሌይ ስቶርያውርዱ

አስኳላ ቀጣይ ፕሮጀክት ነው ተጨማሪ ይዘቶች እና ጨዋታዎች በምርት ሂደት ላይ

አስኳላ ተጨማሪ ይዘቶችን እና ጨዋታዎችን ማካተቱን እና ማደጉን ይቀጥላል። በአሁኑ ጊዜ የግዕዝ ቁጥሮችን ፣ ቅርጾችን ፣ ቀለሞችን ፣ የአካል ክፍሎችን ፣ መደመርን ፣ መቀነስን እና ተጨማሪ ቃላትን ወደ ነባር ጨዋታዎች ለማከል እና አዳዲስ አገራዊ ቋንቋዎችን በመጨመር በስልክዎ ውስጥ የሚገኝ የተሟላ የተሟላ መዋለ ህፃናት ደረጃ ለማድረስ እየሰራን ነው። ተጨማሪ የዕድሜ ክልሎችም እና የዕውቀት ከባቢዎችን በማካተት የጨዋታውን ይዘቶች ማሳደግ እንቀጥላለን

Actually 5 star is not enough for this app, I have download this app today. its really awsm, and i didn't keyed this much of words to any app.good job.

Abebaw Abebe

AWESOME app! I love having a free, easy, nice graphics, good looking and a professional ways of teaching kids... Thanks for sharing !

Dereje Birhanu

It is really helpful and interacting app to my kids. My daughter is already enjoying it. I am happy to see such learning apps for kids...

Soniti Mos

አስኳላ ቀላል የመማሪያ መንገድ ነው

አስኳላ 11 በ 1 ትምህርታዊ ጨዋታዎች ለልጆች ፣ ለአጸደ ህጻናት ተማሪዎች ፣ ለኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች እና አማርኛን የማዳመጥ ፣ የማንበብ እና የመፃፍ መሰረታዊ ክህሎቶችን ለማሳደግ ለሚፈልግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው

ስለ አስኳላ አዳዲስ መረጃዎችን ያግኙለአዳዲስ መረጃዎች እዚህ ይመዝገቡ

አስኳላን ከጎግል ፕሌይ እና ከአፕ ስቶር በማውረድ አማርኛ የመስማት የማንበብ እና የመጻፍ ክህሎቶን ያሳድጉ

ከአፕ ስቶርያውርዱከፕሌይ ስቶርያውርዱ